
የያዬ ከለማ ማዘጋጃ ቤት
ስለ ያዬ ከተማ በጥቂቱ
ጥንታዊው የያዬ ከተማ የተቆረቆረው በ1888ዓ.ም ሆኖ የማዘጋጃ ቤትነት ዕቁቅና ያገኘዉ ድግሞ በ1935ዓ.ም እንደሆነ ታሪክ ይናገራል። የያዬ ከተማ በሰባት ቀበሌዎች፣ በ28 መንደር እንዲሁም 2007ብሎኮች የተዋቀረ ከተማ ነው። የከተማው የህዝብ ከ63, 938 በላይ ሲሆን በ2587 ሄክራር በአጠቃላይ የተከማው ስፋት ሰፍሮ ይገኛል።የያዬ ከተማ ከባህር ወለል በላይ በአማካይ 2500ሜትር በላይ የሚገኝ ሲሆን በአየር ንብረቱ ደጋማ ሆኖ በዓመት በአማካይ ከ1400-1600ሚሊ ሜትር ዝናብ ያገኛል።
በያዬ ከተማ ምንም እንኳን በሲዳማ ክልል ውስጥ የሚገኝ ከተማ ቢሆንም የበርካታ ብሔር ተወላጆች ከሲዳማ ህዝብ ጋር ተዋደው፣ ተጋብተውና ተዋልደው በፍቅር የሚኖሩት የትንሿ ኢትዮጵያ ነፀብራቅ ከተማ ነው። በከተማው የኦርቶዶክስ፣ የኢስልም፣ የፕሮቴስታንት እና የባህላዊ እምነት ተከታይ ነዋርዎች በአንድነት በመቻቻል የሚኖሩት ከተማ ነው።
የከተማዉ ልዩ መገለጫ
በቱርዝም ዘርፍ: ያዬ ከተማ እምቅ የቱሪዝም አቅም ያለው ከተማ ነው። በማህበረሰብ ቱሪዝም እየለማ ያለው የጋራምባ ተራራ ከያዬ ከተማ በ14 ኪ.ሜ በቅርብ ርቀት ላይ ይገኛል። የሀፉርሳ ተራራ በያዬ ከተማ ራስገ ለከተማው ልዩ ውበት የሰጠ ነው። ከተማውን በቀኝና በግራ በሁለት ጎሮንቴና ጣሬ ወንዞችና ፏፏቴዎች የተከበበ ነው። በከተማው ዙሪያ ለቱሪዝም የተከለሉ የሚሊኒየም ፓርክ፣ ግድብና ያዬ ስታዲየም ዙሪያና ችግኝ ጣቢያው በእራሱ ልዩ የቱሪስት መዳረሻ ነው።በባህል ዘርፍ፡ አከባቢው በሲዳማ ቱባ ባህል መገኛነት የሚታወቅ ሲሆን በያዬ ከተማ ራስጌ ሚሊኒየም ፓርክ የሲዳማ ባህላዊ ዳኝነት የሚካሄድበትን የሶንጎ ስፍራ ይገኛል።በስፖርት ዘርፍ፡ ያዬና አከባቢው ለስፖርት እንቅስቃሴ የሚመች በተፈጥሮና የአየር ፀባይ ያለው ከተማ ነው። በተፈጥሮ ተራራዎች የተከለለው የያዬ ስታዲየም ለስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችና ለተለያዩ ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊና የመንግሥት ኩነቶች ምቹ ሥፍራ ነው።ከተማው በሁለት ወንዞች መካከል የሚገኝ ልዩ ስታዲየም ባለቤት መሆኑ ለስፖርት ልማት የሚመች ነው። በተለይም በአትሌትክስ ዘርፉ በ3000ሜትር የመሰናክል ሩጫ የኢትዮጵያን ስንደቅ ዓላማ በዓለም አደባባይ ከፍ ያደረጉ አትሌት ሳሙኤል ፍረው የመሰሉ አትሌቶች ያፈራ፣ በሲዳማ ቡና፣ በቦቆጂ እና ለአርስ አትሌትክስ ክለብ ጥሩ ውጤት እያስመዘገቡ ያሉ በርካታ አትሌቶችን ያፈራ ከተማ ነው።በኢንቨስትመንት፡- ከተማችን በተፈጥሮ ፀጋ ባለበት በመሆኑ ከገረንባ ተራራ የሚፈልቁ የከርሰ ምድር ምንጮች ባለቤት በመሆኑ በታሸገ ውሃ ኢንቨስትመንት አገልግሎቱን ከጀመረው የሳውዝ ስፕርንግ የውሃ ፋብሪካ ጨምሮ በግንባታ ላይ የምገኙ ከአራት የውሃ ፋብሪካዎች ግንባታ ላይ ናቸው። የያዬ ከተማ በሆተልና ቱርዝም ዘርፉ እምቅ አቅም ያለው ሲሆን በሆቴል እንቨስትመንት ወደ ሥራ የገቡ ባለሀብቶች ያሉበት ከተማ ነው።ወረዳው በዓለም ተወዳዳሪ የሆነ የስፔሻሊት ቡና አብቃይ ሲሆን ከሦስት ጊዜ በላይ በዓለም የልህቀት ደረጃ ቡና ማሸነፍ የቻለ ነው። ይህም ለከተማው በግብርናውና ኢኮኖሚ ዘርፍ ከፍተኛ መነቃቃትን መፍጠር ችሎአል።
በከተማዉ ትምህርትእና ጤና አገልግሎት በተመለከተ
በትምህርት ዘርፍ፦ የያዬ ከተማ ዋና መገለጫዋ ትምህርት ሲሆን፤ ከተማው 1937 ዓ.ም የተመሠረተ ታሪካዊው የአርቤጎና ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ቀዳሚ ትምህርት ቤት ባለቤት ነው። ከዚህ አከባቢ በርካታ የተማሩ የተመራመሩ ተማሪዎች የወጡ ሲሆን ለአብነት የኢጋድ ዋና ፀሐፍ ዶ/ር ወርቅኔ ገበዬሁ፣ አምባሳደር ደ/ር ማርቆስ ተክሌ፣ የሐዋሳ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች ዶ.ር ታፈሰ ማቴዎስ፣ ዶ.ር ሳሙኤል ጅሎና ሌሎችም በርካታ ምሁራን ያፈራ ከተማ ነው። በከተማው የትምህርት ስርጭቱን ስንመለከት ቅድሜ አንደኛ ት/ቤት 3፣ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 6 ፣የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት 3 እና አንድ ቴክንክና ሙያ ኮሌጅ ይገኛል። በእነዚህ የትምህርት ተቋማት በአጠቃላይ ከ12074 ሺህ ባለይ ተማሪዎች ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል።በጤናው ዘርፍ፡- የአንድ ከተማ ማህበረሰብ ዋነኛ ተግባር ጤናው የተጠበቅ ምርታማና አምራች ማህበረሰብ በመፍጠር የከተማውን ለውጥና እድገት ማረጋግጥ ነው። በዚህ ረገድ የያዬ ከተማ አንድ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልና አምስት ጤና ኬላ ያለው ሲሆን የህብረተሰቡን በሽታ የመከላከል ፖሊስ ተግባራዊ በማድረግ የጨቅላ ህጻናትና የእናቶችን ሞት በእጅጉ የቀነሰ፣ ከፍተኛ የከተማ የጤና ሠራዊት በየመንደሩና በየብሎኩ በመፍጠር የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ ብርቱ ጥረት እያደረገ የሚገኝ ከተማ ነው።በአከባቢ ጥበቃና አርንጓዴ ልማት ዘርፍ፦ የአረንጓዴ አሻራ ልማት የያዬ ከተማ ገፅታ ነው። ከተማው በአረንጓዴ እፅዋትና የተሸፈነና በወንዞች የተከበበ ነው። ያዬ ከተማ ማዘጋጃ ለነዋርዎቿ ምቹ ከተማ ለመፈጠር በአከባብ ጥበቃና በአርንጓደ ልማት ሥራ በከፍተኛ ሁኔታ እየሠራ ይገኛል። በዚህም ተግባር በአጠቃላይ በከተማዉ ውስጥ ብቻ 6 ፓርክ ወደ 65.77ሄክታር የምሸፍን፣ 5 ግርነር 1ሄክታር የሚሸፍን እና አንድ ጥቅብቅ የሀፉርሳ ተራራ ደን 5ሄክታር ማልማት የቻለ ነው። ከተማው ለአካባቢ አረንጓዴ ልማት ሳምባ የሆነውን አንድ ችግኝ ጣብያ 1.5 ሄክታር የሆነ ያለው የአረንጓዴ ልማት ሞዴል መሆን የሚችል ከተማ ነዉ፡፡
የያዬ ከተማ ማዘጋጃ
ራዕይ፡
በ2030 ዓ.ም የያዬ ከተማ በኢኮኖሚ ተወዳዳሪ፣ በተክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት አሰጣጡ ቀልጣፋ፣ በመሠረተ ልማቱ ዘመናዊና ተደራሽ፣ለነዋሪዎቹ ምቹና ማራኪ እንዲሁ አረንጓዴ የቱርዝም ከተማ ሆኖ ማየት፡፡
ተልዕኮ:
በተክኖሎጂ የተደገፈ ፈጣንና ፍትሐዊ አገልግሎት በመስጠት የኢንቨስትመንትና የቱርዝም ዘርፉ የስራ ዕድል ፈጠራን በማበረታታት እንዲሁም በአረንጓዴ ልማት የዳበረ ጽዱና ማራኪ በጠንካራ የህብረተሰብ ተሳትፎና ተጠቃምነትን በማረጋገጥ መሰረተ ልማትን በሟሟላት የነዋሪዎች ኑሮ ጥራት ማሻሻል
እሴት :
- ፍታዊነት
- ግልጸኝነት
- ተጠያቅነት
- እኩልነት
- ሚስጥር ጠባቅነት
- የኢኮኖሚና ኢንቨስትመንትን መፍጠር
- የሥራ ዕድል ፈጠራ
- የገበያ ትስስር
- የከተማ ጽዳትና አርንጓደ ልማት
- የዲጅታል አገልግሎት
- የህብረተሰብ ተሳትፎ
- የባህልና ቅርስ ጥበቃ
